Our Gift to You: Download HOLIDAY RECIPES from our international team members.

በየጊዜው እያንዳንዱ ድርጅት ለእሱ የበለጠ አስተዋፅኦ ባደረጉ ሰዎች እየተቀረፀ እና እነኛን ሰዎች እየመሰለ ይሄዳል፡፡ እኔም ኢንተርናሽናል ሳማሪታንን  በጣም ከምወድበት አንዱ ምክንያት ድርጅቱ የ84 ዓመት የእድሜ ባለፀጋ የሆነችውንና እጅግ ታማኝ የሆነችውን ሴት ስለሚመስል ነው፡፡

ፓውሊን እኤአ በ1938 በበርማ (የአሁኗ ማያንማር) ተወለደች። የሁለተኛው የዓለም ጦርነት ውድመት በመላው ዓለም መስፋፋቱን ተከትሎ፣ የፓውሊን ቤተሰብ በመጀመሪያ ወደ ቻይና ከዚያም ወደ ሕንድ ለደህንነት ተሰደዱ። ወላጆቿ ለእሷና ለሰባት የቤተሰብ አባላት የሚበሉትን ምግብ ያገኙ ዘንድ  ጠንክረው ሠርተዋል፡፡ ፓውሊን በሦስት ዓመት እድሜዋ ከቤታቸው ፊት ለፊት ተቀምጣ ከአራት ዓመት እህቷ ጋር ወላጆቿ ከሥራ ወደ ቤት የሚመለሱበትን ሰዓት በደስታ ስትጠባበቅ እንደነበር ታስታውሳለች።

“በመንገድ ላይ ሩዝ እየሸጠ የሚሄድ አንድ ሰው ነበረ” ትላለች “ይህ ሰውዬ  ሁልጊዜ ለእኔ እና ለእህቴ አንድ ሳህን ሩዝ ይሰጠን ነበር። በእርግጥ ለምን እንዲህ እንዳደረገ አላውቅም። ምናልባት ፈገግ ብለን ‘ሰላም’ ብለነው ሊሆን ይችላል። ግን ያ በጣም ደስ የሚል ነበር። ወላጆቼ ይህንን ሲያውቁ ግን መልሰው ይከፍሉት ነበር። በዚያን ጊዜ የነበረው ሁኔታ ልክ እንደዚያ ነበር”

ፓውሊን እና ታላቅ እህቷ ካሮሊን

ከጦርነቱ በኋላ የፓውሊን ቤተሰቦች እዚያው ማሌዥያ ውስጥ መኖር ቀጠሉ፡፡ አንድ ህይወትን የሚቀይር ክስተት ባይኖርና የኮሌጅ ስኮላርሺፕ እድል ባታገኝ ኖሮ የእሷም መኖሪያ በዚያው ይሆን ነበር፡፡

ልክ እንደ አንዱ  የእኛ የስኮላርሺፕ ተማሪ፣ ፓውሊንም  የወደፊት ህይወቷን የቀየረውን ያንን የስኮላርሺፕ /የነፃ ትምህርት ዕድል ተጠቅማለች።

ፊዚካል ቴራፒስት ሆና በመጨረሻም እኤአ በ1967 ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ፈለሰች፡፡ እናም መኖሪያዋን  በአን አርበር በማድረግ  በሴንት ጆ ሆስፒታል ለ23 ዓመታት ያህል ሰርታለች። በተጨማሪም ድርጅታችንን በመደገፍና ወደተለያዩ የማህበረሰቦቻችን ከተሞችና ሀገራት በመጓዝ ድርጅታችን ከቶሌዶ ወደ አን አርበር ከተጓዘበት እኤአ 2008 ጀምሮ ያላሰለሰ ድጋፍ ስታደርግ ቆይታለች።

በኪፕሊንግ አገላለጽ፣ ፓውሊን “ይቅር የማይባለውን አንድ ደቂቃ በስልሳ ሰከንድ የርቀት ሩጫ” ሞልታዋለች። በአፍሪካ ውስጥ ላሰብነው የማስፋፊያ ፕሮግራም ያሉ መልካም አጋጣሚዎችን ለመቃኘት እንዲረዳን አንድሩ ፓውክ ወደ ኢትዮጵያ ያደረገውን ጉዞ አጅባ  ነበር ወደ ኢትዮጵያ ያቀናችው፡፡ለእርሷ የዚህ ጉዞ ዋና ድምቀት ደግሞ ድንቅ የሆነው እና ሯጩ የእኛ የስኮላርሺፕ ተማሪያችን ምህረቱ ነበር፡፡

“በየዕለቱ ከለሊቱ 10፡00 ሰዓት ገደማ ወደ ትምህርት ቤተ ከመሄዱ በፊት ለመሮጥ ይነሳል፡፡ ይህንን ማመን ትችላለህ?” ፓውሊን ጠየቀችኝ። ፓውሊን ከማውቃቸውና በጣም ትጉህ ከሆኑ ሰዎች መካከል አንዷ ነች፣ በየማለዳው 11፡30 ላይ ከእንቅልፏ ነቅታ ቅዳሴ በመከታተል  ብዙ ሰዎች ወደ ስራ ሲሄዱ ቀድማቸው ትደርሳለች፡፡ ሁልጊዜ ማታ ወደ መኝታ ከመሄዷ በፊት የሰውነት እንቅስቃሴ ትሰራለች፡፡ እንደሚመስለኝ ይህች ሴት በዚህ አይነት ለመጀመሪያ ጊዜ ባገኘችውና የስራና የየዕለት እንቅስቃሴውን ባየችው በዚህ ወጣት ልጅ የተፈተነችና ከእሷም ትጋት የበለጠባት ይመስለኛል፡፡

ማንም በሁለተኛ ቦታ መሆን የለበትም በማለት ፓውሊን አረጋገጠችልኝ  “የ እሱ ክብደት 44 ኪሎ ግራም ነው። እኔ ደግሞ ገና 43 ኪሎግራም ነው የምመዝነው፣ ስለዚህም እጁን ቆንጠጥ አድርጌ ‘ወፍራም ነህ እሺ!’ አልኩት።

ፓውሊን መሳቅ ትወዳለች እናም ሁል ጊዜ ሳቋን ቀጥታ ነው የምትሰጠው። እናም  የእኛ ተልእኮም ለእሷ ጥልቅ ግላዊ ነው።

“አንዳንድ እቃዎች ያስፈልጉት ነበርና ወደ ሰፖርት አልባሳት መሸጫ ሱቅ ይዘነው ሄድን፡፡ እኔም ለሩጫ የሚያገለግሉትን አልባሳት እንዲወስድ ነገርኩት፡፡ ይህ ወጣት 20 ዓመቱ ነው እናም በህይወት ዘመኑ ጥሩ የሆኑ እቃዎችን ለመግዛት እንደዚህ ውድና ጥሩ እቃዎች ወዳሉበት ሱቅ ሲገባ ይህ የመጀመሪያው ነበር፡፡

በጣም የሚያሳዝን ነገር ነው”  ፓውሊን ሀሳብዋን አካፈለችኝ፡፡ በዚያ ጉዞዋ ፓውሊን ለምህረቱ ለሩጫ የሚያስፈልጉትን ትጥቆች ሁሉ ገዝታ በመስጠት ጥሩ ነገር አድርጋለታለች፡፡ የካቲት 5 ቀን 2015 ዓ/ም በሀዋሳ በሚዘጋጀው የታላቁ ሩጫ የግማሽ ማራቶን ውድድር ላይ ትልቅ ውጤት ለማምጣትና በትልልቅ ክለቦች ለመታቀፍ ይሳተፋል፡፡ እናም በዚህ ውድድር ላይ የዛሬ 80 ዓመት ገደማ ያ በጎዳና ላይ ሩዝ እየሸጠ በመስፈሪያ ይሰጣት የነበረውን ሰውዬ ውለታ በማትረሳውና እስከዛሬም ድረስ በምታስታውሰው ፓውሊን የተገዛለትን አዲስ የመሮጫ ጫማና የሩጫ ትጥቆቹን ለብሶ ትልቅ ውጤት ለማስመዝገብ በልምምድ ላይ ይገኛል፡፡

ምህረቱ እና ፓውሊን

Mike Tenbusch, IntSam President

ማይክ በትውልድ ከተማው በዲትሮይት፣ ሚቺጋን ከሁለት አስርት አመታት የማህበራዊ ለውጥ ጥረቶች በኋላ በ2018 አለም አቀፍ ሳምራዊን ተቀላቅሏል። እሱ ከሚቺጋን የህግ ትምህርት ቤት ዩኒቨርስቲ የተመረቀ እና የጆናታን ኢፌክት፡ ልጆች እና ትምህርት ቤቶች በድህነት ላይ የሚደረገውን ጦርነት እንዲያሸንፉ መርዳት ነው። እሱና ባለቤቱ ማሪትዛ በወጣትነት የሚቆዩ ሦስት ልጆች አሏቸው።

You Are There

You Are There

When a landslide tore through the Kiteezi dumpsite in Uganda last weekend, the team you support...

The Victorious One

The Victorious One

There was a swift knock on our car window. A beautiful young girl was standing firmly by the car....

30 Large

I’ve been with International Samaritan for six years now, or a mere 20% of our history, and I want...

Picking for School Supplies

This is Nayeli (pictured above), or “Naye” as we affectionately call her. She lives in the Buen...

America, Remember Who You Are

At the top of my emails this past Monday was this message to Andrew Pawuk, our vice president, and...

Growing Together

In early May, 12 of us from St. Mary Student Parish in Ann Arbor traveled to Honduras to spend a...