

ሐሙስ ዕለት ወደ ዋሽንግተን ዲሲ በአውሮፕላን እየተሳፈርኩ ሳለ ከቡድናችን መሪዎች አንዱ አስደንጋጭ የስልክ ጥሪ ደረሰኝ። “ፍሬዲ” እና ስድስት ጓደኞቹ እሁድ ዕለት እግር ኳስ ለመጫወት እንደሄዱ እና ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እንደጠፉ ነገረችኝ (ስሙ እና ሀገሩ ለደህንነት ሲባል ተቀይሯል)። ስልኮቻቸውን እና ንብረቶቻቸውን እቤት ውስጥ ትተው ስለሄዱ ከሀገር የወጡ አይመስልም። ፍሬዲ ከስኮላርሺፕ ተጠቃሚዎቻችን አንዱ ነው፣ እና እሱ እና ጓደኞቹ ጥሩ ልጆች ናቸው፣ ችግር የሚፈጥሩ አይነትም አይደሉም፣ ስትል ገለፀችልኝ።
የፍሬዲ አባት በጣም አዝኗል። ለሶስት ቀን አልበላም። የጥበቃ ሰራተኛ ነው እናም በቅርቡም ዝርፊያ ለመከላከል ሲል ጥቃት ደርሶበታል። ሌቦቹ እግሩን ሰብረው ሁለት ጥርሱን አውልቀው ነው የሄዱት ። በደረሰበት ጉዳት ላይ የልጁ መጥፋት ተጨምሮ ምን ያህል ስቃይ ላይ እንደነበር መገመት አልችልም።
ፖሊስ ምንም አልረዳም ነበር። ሰባት ወንዶች ልጆች አንድ ላይ ሊጠፉ ይችላሉ በሚለው ሀሳብ ተሳሳቁ እና የፍሬዲ አባት እና ቡድናችን ይህንን ወደ እነሱ ማቅረባችንን እንደ ችግር አዩት።
አውሮፕላኑ ውስጥ በድምጽ ማጉያ ስልኬን እንዳጠፋ ሲነገረኝ፣ ለቤተሰቦቼ እና ለአንዳንድ የአለም አቀፍ ሳማሪታን ጸሎት የሚያደርጉ ደጋፊዎች ስለ ፍሬዲ ጸሎት እንዲያረጉ የሚጠይቁ የፅሁፍ መልክቶችን ላኩኝ።
አሁን አንድ ሳምንት ሆኗል፣ አሁንም ፍሬዲ እና ጓደኞቹ የት እንዳሉ ምንም መረጃ የለንም። ግን መጸለይ ከጀመርንበት ቀን ጀምሮ የሆነ ነገር ተለውጧል። ፖሊሶች ከመሳለቅ ይልቅ ወዲያውኑ ተባባሪዎች ሆነዋል፣ እና የፍሬዲ አባት እንደገና እንዲበላ የሚያረግ ሰላም ተሰማው። ጸሎታችን ለሰባቱ ወንዶች እና ለቤተሰቦቻቸው አንድ እና ጠንካራ ሆኖ ይቆያል።
ቤት ስደርስ አንድ ጥሩ ጓደኛዬን ደወልኩለት አባ. ፍራንክ ካንፊልድ፣ ኤስጄ፣ የ87ኛ ልደቱን ካከበረ በኋላ እንኳን የጽሑፍ መልእክት መላክን አልተለማመደም። ለፍርድዲ እንዲፀልይ ጠየኩት፣ እና “አዎ፣ ሚካኤል፣ በእድሜዬ ጥሩ ማድረግ የምችለው መጸለይ ነው” አለኝ።
ነገሩ እንዲህ ነው፡ ጸሎት በማንኛውም እድሜ በደንብ ማረግ የምንችለው ነገር ነው።
በጸሎት ድጋፍ እንድትሰጡ ከተጠራችሁ፣ እኔ እና አባ ፍራንክ ያለንበት ለስኮላርሺፕ ተጠቃሚዎቻችን እና ቤተሰቦቻቸው የሚፀልዩ ሰዎችን እንድትቀላቀሉ እጋብዛቹሀለሁ። ይህ የሚሆን ከሆነ እባኮትን ኢሜል ላኩልኝ፣ እና በቋሚነት ልባም እና አስቸኳይ ጸሎቶችን ወደሚያገኙ ልዩ ቡድኖች ይቀላቀላሉ ።
እንደ አንድ ምሳሌ፣ በዚህ ሳምንት ማቲዮ ፣ ከ9 አመቱ ጀምሮ በሉኪሚያ ሲጠቃ ቆይቶ አሁን ደግሞ በ15 አመቱ ካንሰር ተመልሶ እንደያዘው ሰማን። አሁን በዊልቸር የሚንቀሳቀስ ሲሆን ቤተሰቡም ተጨማሪ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ። በገንዘብ መርዳት ከፈለጋችሁ፣ እባኮትን እዚህ ይለግሱ እና በአስተያየት መስጫ ሳጥን ውስጥ “Matheo” ብለው ይፃፉ። በጸሎት ውስጥ Matheo እና ቤተሰቡን የሚያስበው ቡድን ውስጥ መሆን ከፈለጉ፣ ለዚህ ኢሜይል ምላሽ በመስጠት ያሳውቁኝ።
እባክዎን ለፍርድዲ እና ለማቲዮ ለመጸለይ ትንሽ ጊዜ ይውሰዱ። የስኮላርሺፕ ተጠቃሚዎቻችን እና ወላጆቻቸው ለሚያስተምሯቸው ሰዎች አብዝተው ይጸልያሉ። በተለይ በዚህ የዐብይ ጾም ወቅት፣ ለእነሱም እንጸልይላቸው።
ለወሳኝ ፍላጎቶች ፈንድ ምስጋና ይግባውና ቡድናችን ማቲዎ ዊልቸር ማግኘት ችሏል።

ማይክ ተንቡሽ, የአለም አቀፍ ሳምራዊ ፕሬዝዳንት
ማይክ በትውልድ ከተማው በዲትሮይት፣ ሚቺጋን ከሁለት አስርት ዓመታት መሪነት ማህበራዊ ለውጥ በኋላ በ2018 IntSamን ተቀላቅሏል። እሱ የሚቺጋን የህግ ተመራቂ እና የጆናታን ውጤት፡ ልጆች እና ትምህርት ቤቶች በድህነት ላይ የሚደረገውን ጦርነት እንዲያሸንፉ የመፅሀፍ ደራሲ ነው። እሱና ባለቤቱ ማሪትዛ በወጣትነት የሚቆዩ ሦስት ልጆች አሏቸው።
A Girl with a Dream Come True Spanish
Doy gracias a Dios por poder ayudar a nuestros beneficiarios y a sus familias y ver sus sonrisas...
Progressive People Unite! AMHARIC
ልጆቼ ልክ እንደ ፕሮጔረሲቭ ማሰታወቂያዎች እንደሚያሾፉባቸው አይነት ሰው ነህ ይሉኛል፡፡ እኔም እስማማለሁ፡፡በእርግጥ ፣ ማሰታወቂያዎቹ ለመጀመሪያ ጊዜ...
Progressive People Unite! SPANISH
Debo confesar que mis hijos me han acusado de ser exactamente igual que las personas de las que se...
A Day Without Water Amharic
በቤትዎ ፣ በቢሮዎ ፣ በሆቴልዎ ፣ በአከባቢዎ ውስጥ ውሃ ለአንድ ቀን ባይኖር ብለው አስበው ያቃሉ? ባይኖር እንጼት እንደሚኖሩ መገመት ይችላሉ? ለአንድ...
A Day Without Water Spanish
¿Puedes imaginarte un día sin agua en tu casa, en tu oficina, en tu hotel, en tu colonia o...
Two Peas in a Pod AMHARIC
በየጊዜው እያንዳንዱ ድርጅት ለእሱ የበለጠ አስተዋፅኦ ባደረጉ ሰዎች እየተቀረፀ እና እነኛን ሰዎች እየመሰለ ይሄዳል፡፡ እኔም ኢንተርናሽናል ሳማሪታንን...