Our Gift to You: Download HOLIDAY RECIPES from our international team members.

እግዚአብሔርም መለሰልኝ እንዲህም አለ። አንባቢው ይፈጥን ዘንድ ራእዩን ጻፍ፥ በጽላትም ላይ ግለጠው። ትንቢተ ዕንባቆም 2፡2

እ.ኤ.አ በ2008 የፀደይ ወቅት ከዲትሮይት ዩናይትድ ዌይ መሪዎች ጋር የሽርሽር ፕሮግራም ላይ ነበርኩ እና በ2030 ዲትሮይት ከተማን ለመስራት እና ለመኖር አመቺ ከሆኑ ምርጥ 5 ከተሞች መካከል አንዷ ለማድረግ “ትልቅ፣ ሰፊና ፣ ደፋር” የሆነ ግብ ነደፍን።

ከሽርሽሩ በኋላ ያንን ግብ በፖስተር ላይ ፅፈን  በስብሰባ አዳራሻችን ግድግዳ ላይ ሰቀልነው። ከጥቂት ወራት በኋላ፣የተከሰተው  የፋይናንስ ውድቀት የክሪስለር እና የጂኤም ኪሳራን አስከተለ፣ እና በመጨረሻም የዲትሮይትን ከተማ። በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችም ስራቸውን አጡ። የቢግ 3 አውቶሞቢሎች መሪዎች ከኮንግረስ የዋስትና ክፍያን በመፈለግ ፈንታ አዋራጅ ሽንፈት ገጥሟቸዋል፣ በመቀጠልም ፍጻሜው – በታይም መፅሄት የፊት ገፅ ላይ በራዕያችን ላይ መሳለቂያ ሆነ።

የታይም ልዩ ዘገባ ስለ ዲትሮይት ከ2009 ዓ.ም

ያ ዓመት እጅግአስከፊ አመት ነበር። በዙሪያችን ካለው ኢኮኖሚያዊ ውድመት አንፃር ስለትልቅ ፣ሰፊውና ፣ደፋሩ ግባችን ብዙም አልተናገርንም ፣ነገር ግን በስብሰባ አዳራሻችን ውስጥ የሚገኘውንና ስለዚህ ግባችን የሚያውጀውን ፖስተር ከግድግዳችን ላይ አውርደነው አናውቅም።

ሁሉም ነገር ተለውጧል፡፡  ሆኖም ቢል ፎርድ ጁኒየር ወደዚያ የስብሰባ ክፍላችን ለመጀመሪያ ጊዜ ገባ፡፡  ቢል ፎርድ ማለት የሄንሪ ፎርድ የልጅ ልጅ እና የፎርድ ሞተር ካምፓኒ ሊቀ መንበር  ሲሆን ቢል ከዋና ስራ አስኪያጃችን ማይክ ብሬናን ጋር ተቀምጦ ስለ ስራችን መነጋገር ጀመሩ። በስብሰባቸውም አጋማሽ ላይ፣ ቢል ቀና ብሎ ያንን በግድግዳችን ላይ የሚገኝ ፖስተር ተመልክቶ፣ “በእውነቱ የዩናይትድ ዌይ ትልቅ ደጋፊ ሆኜ አላውቅም፣ ነገር ግን ዲትሮይትን ለመስራት እና ለመኖር አመቺ ከሆኑ ምርጥ ከተሞች መካከል አንዷ እንድትሆን ከልብ የምትፈልጉ ከሆነ፣ ማንኛውንም መርዳት የምችለው ነገር ካለ ለማድረግ ዝግጁ ነኝ አለው፡፡”

በእሱ ማበረታቻ  ወደዚያ ራዕይ ተጠጋን፡፡ እናም ቢል እና ባለቤቱ ሊሳ ቃሉን አክብረው፣ ለጋስ የሆኑ አዳዲስ ደጋፊዎችን በማበረታታት፣ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሰዎች ተጨመሩ፡፡ ሁሉም ጥረቶች እና ጸሎቶች በከተማዋ ለውጥ ላይ ያተኮሩ ነበሩ። . ልክ ባለፈው ሳምንት በ2022፣ ታይም መፅሔትም የመጣውን ለውጥና ተፅእኖ ተመልክቷል።

ታይም መጽሔት በ2022 አዲስ እይታ ነበረው።

ግቦችዎን በመፃፍ ውስጥ ኃይል አለ

ባለፈው አመት ልክ በዚሁ ወቅት የስራ አመራር ቦርዳችን ለዓመታዊ ውሎአችን ተሰብስቦ ሳለ አንድ የጻፍነው የመጀመሪያው ግብ ቀላል ነበር፡ እሱም ንጹህ ውሃ የሚል ነበር። ንፁህ የመጠጥ ውሃን በኢትዮጵያ ውስጥ ቆሬ በመባል ወደሚታወቀው ወደ አፓርታማ  ማህበረሰብ በማምጣት ያስተዋልነውን አስደናቂ ለውጥ በመመልከታችን ይህንን ልምድ በመውሰድ ምንም እንኳን ባለፈው አመት በጀታችን ውስጥ ባይኖርም ለሌላው አጋር ማህበረሰባችን ለማድረግ ግብ አውጥተናል። እንደ እርስዎ ባሉ ከ1,000 በላይ ሰዎች በታላቁ IntSam Global 5K ውስጥ በመሮጥ ወይም በመደገፍ፣ በሆንዱራስ በቡኤን ሳማሪታኖ ማህበረሰብ  በቴጉሲጋልፓ፣ ሆንዱራስ ውስጥ በ 400 ቤቶች ውስጥ ለሚኖሩ 2,000 ለሚሆኑ ሰዎች ንጹህ የመጠጥ ውሃ ለማምጣት የከርሰ ምድር ውሃ ስርዓት በማስገንባት ላይ እንገኛለን። .

እነዚህን ታሪኮች የማካፍላችሁ የ2023 አዲስ ዓመት ግብዎን ወይም ግቦችዎን እንዲጽፉ ለማበረታታት ነው።  ግቦችዎን በመፃፍ በማቀዝቀዣዎ (ፍሪጅዎ) ላይ ወይም በስራ ገበታዎ ዴስክ ፊትለፊት ይስቀሉት እና ለስኬቱ ጓደኞችዎ እንዲጸልዩላቸው ይጠይቋቸው። ከዚያም ጠንክረው ይስሩ እና በዓመቱ ውስጥ የሚሆነውን ይመልከቱ። በህይወትዎ ውስጥ እንደ ተአምር የሚመስል ነገር ቢከሰት አይደነቁ፡፡

በቤቶች ዙሪያ የቧንቧ መስመሮችን የሚቆፍሩ ሰራተኞች

Mike Tenbusch, Presidente de IntSam

Mike የሚቺጋን የህግ ትምህርት ቤት ምሩቅ፣ የ Think Detroit ተባባሪ መስራች እና የጆናታን ኢፌክት ደራሲ ነው። ቀደም ሲል የSAY Detroit Play Center ዋና ዳይሬክተር፣ የዲትሮይት ወላጆች አውታረ መረብ ጊዜያዊ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆኖ አገልግሏል፣ እና የዲትሮይትን የምረቃ ዋጋዎችን ለማሳደግ የዩናይትድ ዌይን ተነሳሽነት መርቷል። በዲትሮይት ውስጥ ድህነትን ለመዋጋት የሠራው ሥራ በውጭ አገር ድህነትን እንዲዋጋ አነሳስቶታል፣ ወደ IntSam መራው። ያም ሆኖ የማይክ ትልቁ ደስታ ባለቤቱ እና ሶስት ልጆቹ ናቸው።

በ2023 የIntSam ግቦች ምን መሆን አለባቸው?

የፊታችን ሀሙስ ቦርዳችን ለ2023 በዓመታዊ የሽርሽር ፕሮግራማችን ግቦችን ያወጣል። የእኛ ራዕይ በማደግ ላይ ያሉ ሀገራት የቆሻሻ ማጠራቀሚያ ስፍራዎች የሰው ልጅ በህይወት ለመኖር የሚታገልበት የማይሆንበት አለም ሲሆን ተግዳሮታችን ደግሞ ወደዛ ራዕይ ለመቅረብ በዚህ አመት ልናስቀምጠው የሚገቡን ሶስት ወይም አራት ዋና ዋና ግቦችን መለየት ነው። እባክዎን ለዚህ ኢሜል ምላሽ በመስጠት በዚህ ዓመት ባለን የሽርሽርና የእቅድ ፕሮግራማችን ልናካትተው የሚገባና እንደ ግብ ልናስቀምጠው የምንችለው ማንኛውም ሀሳብ ካለዎት ያካፍሉኝ፡፡

ትኩረት አለማቀፍ የሳምራውያን ስኮላርሺፕ ተማሪዎች!

ከስኮላርሺፕ ተማሪዎቻችንም መስማት እንፈልጋለን። ከዚህ ሳምንት ጀምሮ ሀሳባቸውን እንዲያካፍሉ በኢትዮጵያ፣ ጓቲማላ፣ ሆንዱራስ፣ ጃማይካ እና ኒካራጓ ላሉ የሁለተኛ ደረጃ እና የኮሌጅ ስኮላርሺፕ ተማሪዎች ሳምንታዊ  አስተንትኖ በስፓኒሽ እና በአማርኛ እንዲያካፍሉን ይላካል።

ተማሪዎች  እባካችሁ ሀሳባችሁን ኢሜል አድርጉልኝ! ለዚህ ኢሜይል ምላሽ በመስጠት በቀጥታ ኢሜል ማድረግ ትችላላችሁ። መልስዎን በጉጉት እጠብቃለሁ፡፡ እናም እባክዎትን ለስራ አመራር ቦርዳችን በዚህ ሐሙስም በሚኖራቸው የውይይት ውሎ ማስተዋልን  እንዲሰጣቸው ጸልዩላቸው።

Will You Dance With Me?

“When you’re dancing, you’re not so concerned about your troubles. You’re asking, ‘Am I in sync...

Go Blue and Red

As we go to the polls in America next Tuesday, I thought you might enjoy the remarks I made at...

Poverty Crushers

Four years ago, I made “a big ask” of a successful business owner and well-respected Catholic...

You’re Not Alone

You're not alone. For our scholars breaking the cycle of poverty, you've found students across the...

See the Change

Never in my life have I seen such profound change in such a short time as the transformation that...

That Was Me

I used to work at the city garbage dump in San Pedro Sula, Honduras. Starting at the age of six, I...