እግዚአብሔርም መለሰልኝ እንዲህም አለ። አንባቢው ይፈጥን ዘንድ ራእዩን ጻፍ፥ በጽላትም ላይ ግለጠው። ትንቢተ ዕንባቆም 2፡2
እ.ኤ.አ በ2008 የፀደይ ወቅት ከዲትሮይት ዩናይትድ ዌይ መሪዎች ጋር የሽርሽር ፕሮግራም ላይ ነበርኩ እና በ2030 ዲትሮይት ከተማን ለመስራት እና ለመኖር አመቺ ከሆኑ ምርጥ 5 ከተሞች መካከል አንዷ ለማድረግ “ትልቅ፣ ሰፊና ፣ ደፋር” የሆነ ግብ ነደፍን።
ከሽርሽሩ በኋላ ያንን ግብ በፖስተር ላይ ፅፈን በስብሰባ አዳራሻችን ግድግዳ ላይ ሰቀልነው። ከጥቂት ወራት በኋላ፣የተከሰተው የፋይናንስ ውድቀት የክሪስለር እና የጂኤም ኪሳራን አስከተለ፣ እና በመጨረሻም የዲትሮይትን ከተማ። በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችም ስራቸውን አጡ። የቢግ 3 አውቶሞቢሎች መሪዎች ከኮንግረስ የዋስትና ክፍያን በመፈለግ ፈንታ አዋራጅ ሽንፈት ገጥሟቸዋል፣ በመቀጠልም ፍጻሜው – በታይም መፅሄት የፊት ገፅ ላይ በራዕያችን ላይ መሳለቂያ ሆነ።
የታይም ልዩ ዘገባ ስለ ዲትሮይት ከ2009 ዓ.ም
ያ ዓመት እጅግአስከፊ አመት ነበር። በዙሪያችን ካለው ኢኮኖሚያዊ ውድመት አንፃር ስለትልቅ ፣ሰፊውና ፣ደፋሩ ግባችን ብዙም አልተናገርንም ፣ነገር ግን በስብሰባ አዳራሻችን ውስጥ የሚገኘውንና ስለዚህ ግባችን የሚያውጀውን ፖስተር ከግድግዳችን ላይ አውርደነው አናውቅም።
ሁሉም ነገር ተለውጧል፡፡ ሆኖም ቢል ፎርድ ጁኒየር ወደዚያ የስብሰባ ክፍላችን ለመጀመሪያ ጊዜ ገባ፡፡ ቢል ፎርድ ማለት የሄንሪ ፎርድ የልጅ ልጅ እና የፎርድ ሞተር ካምፓኒ ሊቀ መንበር ሲሆን ቢል ከዋና ስራ አስኪያጃችን ማይክ ብሬናን ጋር ተቀምጦ ስለ ስራችን መነጋገር ጀመሩ። በስብሰባቸውም አጋማሽ ላይ፣ ቢል ቀና ብሎ ያንን በግድግዳችን ላይ የሚገኝ ፖስተር ተመልክቶ፣ “በእውነቱ የዩናይትድ ዌይ ትልቅ ደጋፊ ሆኜ አላውቅም፣ ነገር ግን ዲትሮይትን ለመስራት እና ለመኖር አመቺ ከሆኑ ምርጥ ከተሞች መካከል አንዷ እንድትሆን ከልብ የምትፈልጉ ከሆነ፣ ማንኛውንም መርዳት የምችለው ነገር ካለ ለማድረግ ዝግጁ ነኝ አለው፡፡”
በእሱ ማበረታቻ ወደዚያ ራዕይ ተጠጋን፡፡ እናም ቢል እና ባለቤቱ ሊሳ ቃሉን አክብረው፣ ለጋስ የሆኑ አዳዲስ ደጋፊዎችን በማበረታታት፣ ስፍር ቁጥር የሌላቸው ሰዎች ተጨመሩ፡፡ ሁሉም ጥረቶች እና ጸሎቶች በከተማዋ ለውጥ ላይ ያተኮሩ ነበሩ። . ልክ ባለፈው ሳምንት በ2022፣ ታይም መፅሔትም የመጣውን ለውጥና ተፅእኖ ተመልክቷል።
ታይም መጽሔት በ2022 አዲስ እይታ ነበረው።
ግቦችዎን በመፃፍ ውስጥ ኃይል አለ
ባለፈው አመት ልክ በዚሁ ወቅት የስራ አመራር ቦርዳችን ለዓመታዊ ውሎአችን ተሰብስቦ ሳለ አንድ የጻፍነው የመጀመሪያው ግብ ቀላል ነበር፡ እሱም ንጹህ ውሃ የሚል ነበር። ንፁህ የመጠጥ ውሃን በኢትዮጵያ ውስጥ ቆሬ በመባል ወደሚታወቀው ወደ አፓርታማ ማህበረሰብ በማምጣት ያስተዋልነውን አስደናቂ ለውጥ በመመልከታችን ይህንን ልምድ በመውሰድ ምንም እንኳን ባለፈው አመት በጀታችን ውስጥ ባይኖርም ለሌላው አጋር ማህበረሰባችን ለማድረግ ግብ አውጥተናል። እንደ እርስዎ ባሉ ከ1,000 በላይ ሰዎች በታላቁ IntSam Global 5K ውስጥ በመሮጥ ወይም በመደገፍ፣ በሆንዱራስ በቡኤን ሳማሪታኖ ማህበረሰብ በቴጉሲጋልፓ፣ ሆንዱራስ ውስጥ በ 400 ቤቶች ውስጥ ለሚኖሩ 2,000 ለሚሆኑ ሰዎች ንጹህ የመጠጥ ውሃ ለማምጣት የከርሰ ምድር ውሃ ስርዓት በማስገንባት ላይ እንገኛለን። .
እነዚህን ታሪኮች የማካፍላችሁ የ2023 አዲስ ዓመት ግብዎን ወይም ግቦችዎን እንዲጽፉ ለማበረታታት ነው። ግቦችዎን በመፃፍ በማቀዝቀዣዎ (ፍሪጅዎ) ላይ ወይም በስራ ገበታዎ ዴስክ ፊትለፊት ይስቀሉት እና ለስኬቱ ጓደኞችዎ እንዲጸልዩላቸው ይጠይቋቸው። ከዚያም ጠንክረው ይስሩ እና በዓመቱ ውስጥ የሚሆነውን ይመልከቱ። በህይወትዎ ውስጥ እንደ ተአምር የሚመስል ነገር ቢከሰት አይደነቁ፡፡
በቤቶች ዙሪያ የቧንቧ መስመሮችን የሚቆፍሩ ሰራተኞች
Mike Tenbusch, Presidente de IntSam
Mike የሚቺጋን የህግ ትምህርት ቤት ምሩቅ፣ የ Think Detroit ተባባሪ መስራች እና የጆናታን ኢፌክት ደራሲ ነው። ቀደም ሲል የSAY Detroit Play Center ዋና ዳይሬክተር፣ የዲትሮይት ወላጆች አውታረ መረብ ጊዜያዊ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆኖ አገልግሏል፣ እና የዲትሮይትን የምረቃ ዋጋዎችን ለማሳደግ የዩናይትድ ዌይን ተነሳሽነት መርቷል። በዲትሮይት ውስጥ ድህነትን ለመዋጋት የሠራው ሥራ በውጭ አገር ድህነትን እንዲዋጋ አነሳስቶታል፣ ወደ IntSam መራው። ያም ሆኖ የማይክ ትልቁ ደስታ ባለቤቱ እና ሶስት ልጆቹ ናቸው።
በ2023 የIntSam ግቦች ምን መሆን አለባቸው?
ትኩረት አለማቀፍ የሳምራውያን ስኮላርሺፕ ተማሪዎች!
ከስኮላርሺፕ ተማሪዎቻችንም መስማት እንፈልጋለን። ከዚህ ሳምንት ጀምሮ ሀሳባቸውን እንዲያካፍሉ በኢትዮጵያ፣ ጓቲማላ፣ ሆንዱራስ፣ ጃማይካ እና ኒካራጓ ላሉ የሁለተኛ ደረጃ እና የኮሌጅ ስኮላርሺፕ ተማሪዎች ሳምንታዊ አስተንትኖ በስፓኒሽ እና በአማርኛ እንዲያካፍሉን ይላካል።
ተማሪዎች እባካችሁ ሀሳባችሁን ኢሜል አድርጉልኝ! ለዚህ ኢሜይል ምላሽ በመስጠት በቀጥታ ኢሜል ማድረግ ትችላላችሁ። መልስዎን በጉጉት እጠብቃለሁ፡፡ እናም እባክዎትን ለስራ አመራር ቦርዳችን በዚህ ሐሙስም በሚኖራቸው የውይይት ውሎ ማስተዋልን እንዲሰጣቸው ጸልዩላቸው።
A New Life for A Graduate
By Mike Tenbusch | February 25, 2022 When we started our strategic planning process in 2019, one...
It’s Time to Go Back to School in Honduras
By Andrew Pawuk | February 18, 2022 Imagine starting school without a uniform, a backpack, or even...
How The 5K Saved My Life
By Mike Tenbusch | February 4, 2022 Last summer, we asked you and everyone else we know across the...
Jumpstart Your Advent
By Mike Tenbusch | December 03, 2021 We’re five days into the Advent season, and it’s not too late...
From Searching to Serving
By Mike Tenbusch | November 26, 2021 Three years ago, Ronia Romero led the expansion of our Paso a...
Que Milagro! We Did It!
By Mike Tenbusch | November 12, 2021 The first donation I ever received was for $25. It was in...
